ነፍሰ ጡር መሆንዎን ማወቅ አስደሳች፣ የማወቅ ጉጉት እና እርግጠኛ ያለመሆን ስሜቶችን ሊፈጥር ይችላል። የወር አበባ መቅረት አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች መጀመሪያ የሚያስቡት ምልክት ቢሆንም፣ የእርግዝና ምርመራ ውጤት ከመታወቁ በፊትም እንኳ እርግዝና በሰውነት ላይ በርካታ ለውጦችን ሊያስከትል ይችላል። እነዚህን ቀደምት ምልክቶች መረዳትዎ፣ ምርመራ ለማድረግ ወይም የጤና ባለሙያን ለመጎብኘት ጊዜው መቼ እንደሆነ ለመለየት ይረዳዎታል። 

ከሁሉ አስቀድሞ የሚታየውና በጣም የተለመደው የእርግዝና ምልክት የወር አበባ መቅረት ነው። ሆኖም ግን፣ ሁሉም ሰው መደበኛ የወር አበባ ዑደት ስለማይኖረው፣ ሌሎች ምልክቶች ጠቃሚ ፍንጮችን ሊሰጡ ይችላሉ። ብዙ ሴቶች በሆርሞን ለውጦች ምክንያት የጡት ህመም ወይም ማበጥ ያስተውላሉ። ጡቶች ከተለመደው በላይ ሊከበዱ ወይም በቀላሉ የህመም ስሜት የሚሰማቸው ሊሆኑ ይችላሉ። 

ድካም ሌላው የተለመደ የቀደምት እርግዝና ምልክት ነው። የፕሮጄስትሮን (progesterone) ሆርሞን መጠን መጨመር፣ በቂ እረፍት እያገኙ ቢሆንም እንኳ ከተለመደው ውጭ የድካም ስሜት እንዲሰማዎት ሊያደርግ ይችላል። አንዳንድ ሴቶች የማቅለሽለሽ ስሜት (በተለምዶ የጠዋት ህመም/እርግዝና ህመም በመባል የሚታወቀው) ሊያጋጥማቸው ይችላል፤ ይህም በቀን ውስጥ በማንኛውም ጊዜ ሊከሰት የሚችል ሲሆን፣ ፅንሱ ከተፈጠረ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሊጀምር ይችላል። 

በተደጋጋሚ መሽናትም በእርግዝና መጀመሪያ ላይ ሊታይ የሚችል ሌላው ምልክት ነው። የሆርሞን ለውጦች እና ወደ ኩላሊት የሚሄደው የደም ፍሰት መጨመር ከተለመደው በላይ በተደጋጋሚ ወደ መጸዳጃ ቤት እንዲሄዱ ሊያደርግ ይችላል። አንዳንድ ሴቶች nuቀላል የሆድ ቁርጠት ወይም መጠነኛ የደም ጠብታ ማየትን ያስተውላሉ፤ ይህም የሚከሰተው የዳበረው እንቁላል የማህፀን ግድግዳ ላይ በሚቀበርበት ጊዜ ነው። 

ሌሎች ቀደምት የእርግዝና ምልክቶች የስሜት መለዋወጥ፣ የሆድ መነፋት፣ ራስ ምታት፣ የተወሰኑ ምግቦችን በጣም መፈለግ ወይም መጥላት፣ እና የሽታ ስሜት መጨመርን ሊያካትቱ ይችላሉ። ምንም እንኳን እነዚህ ምልክቶች በሌሎች የጤና ሁኔታዎች ምክንያት ሊከሰቱ ቢችሉም፣ በርካቶቹን በአንድ ላይ ማስተዋል ግን እርግዝናን ሊያመለክት ይችላል። 

ምልክቶቹ ከሰው ወደ ሰው እንደሚለያዩ ማስታወስ አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ሴቶች ብዙ ቀደምት ምልክቶች ሲታዩባቸው፣ ሌሎች ደግሞ በጣም ጥቂት ምልክቶችን ብቻ ያስተውላሉ። እርግዝናን በእርግጠኝነት ለማረጋገጥ በጣም አስተማማኙ መንገድ የእርግዝና ምርመራ ማድረግ እና በመቀጠልም ከጤና ባለሙያ ጋር መማከር ነው። 

ነፍሰ ጡር መሆንዎን ካሰቡ፣ የወር አበባዎ ከቀረ በኋላ ምርመራ ማድረግ እና ቀደምት የቅድመ ወሊድ ክትትል መጀመር፣ ለእርስዎም ሆነ ለሕፃኑ ጤናማ እርግዝና እንዲኖር ለመርዳት ጠቃሚ ነው። ቀደምት ክትትል ስለ አመጋገብ፣ ስለ ፎሊክ አሲድ ንጥረ ነገር አወሳሰድ፣ ስለ አኗኗር ዘይቤ ምርጫዎች እና የእርግዝና ውጤቶችን ሊነኩ ስለሚችሉ ማናቸውም የጤና ስጋቶች ለመወያየት ዕድል ይሰጣል። 

 

Discovering that you might be pregnant can bring a mix of excitement, curiosity and  uncertainty. While a missed period is often the first sign people think of, pregnancy can cause several changes in the body even before a pregnancy test turns positive. Understanding these early signs can help you recognize when it may be time to take a test or visit a healthcare provider. 

One of the earliest and most common signs of pregnancy is a missed menstrual period. However,  not everyone experiences regular cycles, so other symptoms may provide important clues. Many women notice breast tenderness or swelling due to hormonal changes. The breasts may feel heavier, more sensitive, or sore than usual. 

Fatigue is another common early symptom. Rising levels of the hormone progesterone can make you feel unusually tired, even if you are getting enough rest. Some people also experience nausea, commonly known as morning sickness, which can occur at any time of the day and may begin as early as a few weeks after conception. 

Frequent urination is another sign that may appear early in pregnancy. Hormonal changes and increased blood flow to the kidneys can cause you to need the bathroom more often than usual. Some women also notice mild cramping or light spotting, known as implantation bleeding, which occurs when a fertilized egg attaches to the lining of the uterus. 

Other early pregnancy symptoms may include mood swings, bloating, headaches, food cravings or aversions, and a heightened sense of smell. While these symptoms can be caused by other conditions, experiencing several of them together may indicate pregnancy. 

It is important to remember that symptoms vary from person to person. Some women experience many early signs, while others notice very few. The most reliable way to confirm a pregnancy is through a pregnancy test followed by consultation with a healthcare provider. 

If you think you may be pregnant, taking a test after a missed period and seeking early prenatal care can help ensure a healthy pregnancy for both you and your baby. Early care provides an opportunity to discuss nutrition, folic acid supplementation, lifestyle choices, and any health concerns that may affect pregnancy outcomes. 

wpChatIcon