ለመጀመሪያ ጊዜ እናት መሆን ማንም ሰው አስቀድሞ የማይነግርሽን የጸጥታ ዓይነት ድንጋጤን ይዞ ይመጣል። ልጅሽን በጥልቀት ትወጃለሽ፣ ሆኖም ግን ሁሉንም ነገር እሳሳታለሁ በሚል ስሜት ትጨነቂያለሽ፣ ትጠራጠሪያለሽ፣ እንዲሁም ትፈሪያለሽ። እነዚህ ስሜቶች መጥፎ እናት አያደርጉሽም። በቀላሉ አዲስ እናት መሆንሽን ነው የሚያሳዩት።
የመጀመሪያዎቹ የወሊድ ማግስት ቀናት ስሜታዊ የሚያደርጉ እና አድካሚ ናቸው። ሆርሞኖችሽ እየተቀያየሩ ነው፣ ሰውነትሽ እያገገመ ነው፣ እና በድንገት የሚፈልገውን ነገር ማስረዳት ለማይችል ትንሽ ሰው ኃላፊነት ወስደሻል። ሳይታሰብሽ ልታለቅሽ ትችያለሽ፣ ህፃኑ ባለቀሰ ቁጥር ጭንቀት ሊሰማሽ ይችላል፣ ወይም እየተቸገርሽ ያለሽው አንቺ ብቻ እንደሆንሽ ልታስቢ ትችያለሽ። ግን ብቻሽን አይደለሽም። እያንዳንዷ አዲስ እናት በራስ የመተማመን ስሜቷ ቀስ እያለ ማደግ ከመጀመሩ በፊት ራሷን በመጠራጠርን ሂደት ውስጥ ታልፋለች። ነገሮችን በዝግታ ማድረግ፣ ጥያቄዎችን መጠየቅ እና ራስሽን ማስተማር አስፈላጊ ነው።
ድጋፍ ማግኘት ከምንም በላይ አስፈላጊ ነው። ከወሊድ በኋላ ያለውን ጊዜ ብቻሽን ልትወጪው አይገባም። ከባልሽ እና ከቤተሰብሽ ድጋፍ አግኚ። ያለምንም የጥፋተኝነት ስሜት እርዳታ ጠይቂ። እረፍት በሚታደርጊበት ጊዜ ሌላ ሰው ህፃኑን እንዲይዝልሽ ፍቀጂ። ምግብን፣ አጋርነትን እና መጽናናትን ተቀበይ። ስለሚሰማሽ ስሜት ማውራት ያጠናክርሻል እንጂ አያዳክምሽም። ድጋፍ ያገኘች እናት ጤናማ እናት ናት ይህ ድጋፍ ደግሞ በቀጥታ ለልጅሽ ይጠቅማል።
ይህን የሽግግር ወቅት ይበልጥ ቀላል የሚያደርጉ መደረግ ያለባቸው እና የሌለባቸው ነገሮች አሉ።
● መደረግ ያለባቸው (Dos)
እረፍት አድርጊ፦በተቻለሽ መጠን እረፍት አድርጊ።
ሰውነትሽን በትክክል መግቢ፦ ሰውነትሽን በንጥረ ነገር ገንቢ።
አጫጭር እረፍቶችን ውሰጂ፦ አጫጭርና ማንም ጣልቃ የማይገባባቸው የእረፍት ጊዜያትን ውሰጂ።
የውስጥ ስሜትሽን እመኚ፦ በሰውነትሽ ወይም በስሜትሽ ላይ ያልተለመደ ነገር ከተሰማሽ የጤና ባለሙያ አማክሪ።
● መደረግ የሌለባቸው (Don’ts)
ራስሽን ከሌሎች ጋር አታነጻጽሪ፦ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ከሚታዩት ተመርጠውና ተስተካክለው ከሚለቀቁት የእናትነት ምስሎች ጋር ራስሽን አታነጻጽሪ።
ፈጣን ለውጥ አትጠብቂ፦ ቤትሽ፣ የዕለት ተዕለት ውሎሽ ወይም ሰውነትሽ ወዲያውኑ ወደ ነበረበት ይመለሳል ብለሽ አትጠብቂ።
ራስሽ ላይ ጫና አታብዢ፦ ሁሉንም ነገር በአንዴ ለማወቅ ራስሽን አታስጨንቂ። በአንድ ጊዜ እያገገምሽም እየተማርሽም ነው፣ ይህ ራሱ ሙሉ ጊዜ የሚወስድ ትልቅ ስራ ነው።
እናትነት ብዙ ጊዜ በድንጋጤም በከፍተኛ ፍቅርም አብሮ ይጀምራል፣ እና ሁለቱም ስሜቶች ተስማምተው አብረው ሊኖሩ ይችላሉ። ጥርጣሬ ሊሰማሽ የሚችልባቸው ጊዜያት ይኖሩሻል፣ ነገር ግን በእያንዳንዱ በሚያልፉት ቀናት እየጠነከርሽ እና በራስ የመተማመን ስሜትሽ እየጨመረ ይሄዳል። ጥሩ እናት ለመሆን ፍጹም መሆን አይጠበቅብሽም።
የሚያስፈልግሽ በአካል እና በስሜት መገኘት፣ ለራስሽ ትዕግስት ማሳየት፣ እና መስመርሽን እስክታገኚ ድረስ ድጋፍን ለመቀበል ፈቃደኛ ብቻ ነው።
Becoming a mother for the first time brings a quiet kind of panic that no one warns you about. You love your baby deeply, yet you also feel overwhelmed, unsure, and afraid of lgetting everything wrong. These feelings do not make you a bad mother. They simply make you a new one.
The early postpartum days are tender, emotional, and exhausting. Your hormones are shifting, your body is healing, and you are suddenly responsible for a tiny person who can’t explain what they need. You might cry unexpectedly, feel anxious every time your baby fusses, or wonder if you are the only one struggling. You are not. Every new mom walks through self-doubt before confidence quietly starts to grow. It is okay to move slowly, ask questions, and give yourself permission to learn.
Support is everything. You are not meant to carry postpartum alone. Lean on your partner, involve your family, and ask for help without guilt. Let someone else hold the baby while you rest. Accept meals, accept company, accept comfort. Talking about how you feel strengthens you, not weakens you. A supported mother is a healthier mother and that support directly benefits your baby.
There are simple dos and don’ts that make this transition gentler. Do rest whenever possible, nourish your body, and take small uninterrupted breaks. Do trust your instincts land reach out to a health provider if something feels off with your body or your emotions. Don’t compare yourself to curated social media motherhood. Don’t expect l your home, routine, or body to bounce back instantly. And don’t pressure yourself to master everything at once. You are healing and learning at the same time, that alone is a full-time job.
Motherhood often begins with both panic and profound love, and the two can comfortably exist together. You will have uncertain moments, but you will also grow stronger and more confident with each passing day. You do not need perfection to be a good mother. You just need presence, patience with yourself, and the courage to accept support while you find your rhythm.