የማህፀን ዕጢ” የሚለውን ቃል ሲሰሙ ወዲያውኑ ከባድ ነገር እንደተፈጠረ ሊያስቡ ይችላሉ። ወይም ደግሞ በምርመራ ወቅት ተገኝቶ ምን ማለት እንደሆነ ግራ ገብቶዎት ይሆናል። ስለ ጉዳዩ በግልጽ ስለማይወራ እንዲህ ዓይነት ስሜት መፈጠሩ የተለመደ ነው።

የማህፀን ዕጢዎች (Ovarian cysts) በእንቁልጢዎች (ovaries) ላይ ወይም ውስጥ የሚፈጠሩ በፈሳሽ የተሞሉ ትንንሽ እባጮች ናቸው። አብዛኛውን ጊዜ እነዚህ ዕጢዎች የሰውነት ተፈጥሯዊ የሥራ ሂደት አካል ናቸው። በወር አበባ ዑደት ወቅት እንቁልጢዎች እንቁላል ያመርታሉ። አንዳንድ ጊዜ በእንቁልጢዎች ዙሪያ ትንሽ ከረጢት ይፈጠርና ወዲያውኑ ሳይጠፋ ይቆያል። እነዚህ “ተግባራዊ ዕጢዎች” (functional cysts) ይባላሉ። አብዛኛውን ጊዜ ምንም ዓይነት ሕክምና ሳያስፈልጋቸው ከአንድ እስከ ሦስት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ በራሳቸው ይጠፋሉ። “ዕጢ” የሚለውን ቃል ሲሰሙ መጨነቅዎ ተፈጥሯዊ ቢሆንም፣ አብዛኞቹ የማህፀን ዕጢዎች አደገኛ አይደሉም፤ በረጅም ጊዜ ጤናዎ ላይም ጉዳት አያመጡም።

ምልክቶች እና ዓይነቶች

ብዙዎቹ የማህፀን ዕጢዎች ምንም ዓይነት ምልክት አያሳዩም። ብዙውን ጊዜ የሚታወቁት ለሌላ ምርመራ በሚደረግ የአልትራሳውንድ ምርመራ ወቅት ነው። ምልክቶች በሚታዩበት ጊዜ ደግሞ በታችኛው የሆድ ክፍል ላይ የመክበድ ስሜት፣ መጠነኛ የሆድ መነፋት ወይም በአንድ በኩል የሚሰማ መለስተኛ ሕመም ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ምልክቶች ከመደበኛው የወር አበባ ሕመም ጋር ሊመታቱ ይችላሉ።

ከወር አበባ ዑደት ጋር የማይገናኙ ሌሎች የዕጢ ዓይነቶችም አሉ። ለምሳሌ፦

 ኢንዶሜትሪዮማ (Endometriomas)፦ ከማህፀን ግድግዳ ውጭ የሚበቅሉ የሕብረ ሕዋስ ችግሮች (endometriosis) ጋር የተያያዙ ናቸው።

ደርሞይድ ዕጢዎች (Dermoid cysts)፦እንደ ቆዳ ወይም ፀጉር ያሉ የተለያዩ የሰውነት ሕብረ ሕዋሳትን ሊይዙ ይችላሉ።

ሲስታዴኖማስ (Cystadenomas)፦ የእንቁላል እጢዎች ወለል ላይ የሚበቅሉ ናቸው።

እነዚህ የቅርብ ክትትል ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ሁሉም ዕጢዎች ተመሳሳይ አለመሆናቸውን መረዳት አላስፈላጊ ፍርሃትን ለመቀነስ ይረዳል።

መቼ ነው ወደ ህክምና ተቋም መሄድ ያለብን?

አብዛኞቹ ዕጢዎች ጉዳት የሌላቸው ቢሆኑም፣ የተወሰኑ ምልክቶች ግን ችላ ሊባሉ አይገባም። የሚከተሉት ምልክቶች ከታዩ አስቸኳይ ሕክምና ያስፈልጋል፦

● ድንገተኛ እና ከፍተኛ የዳሌ ወይም የሆድ ሕመም።

● ከሕመም ጋር ተያይዞ የሚመጣ ትኩሳት ወይም ማቅለሽለሽ/ማስመለስ።

● ፈጣን አተነፋፈስ፣ ማዞር፣ ወይም የሰውነት መቀዝቀዝ (ይህ ዕጢው ሲፈነዳ ወይም እንቁልጢው ሲጠቀለል/Torsion ሊከሰት ይችላል)።

አንድ ዕጢ በአልትራሳውንድ ከተገኘ፣ የተለመደው አካሄድ በጊዜ ሂደት መከታተል (watchful waiting) ነው። የወሊድ መከላከያ ሆርሞኖች አዳዲስ ዕጢዎች እንዳይፈጠሩ ሊረዱ ይችላሉ እንጂ ያሉትን አያጠፉም። ቀዶ ጥገና የሚታሰበው ዕጢው በጣም ትልቅ ከሆነ፣ ሳይጠፋ ከቆየ ወይም ከባድ ሕመም ካስከተለ ብቻ ነው።

የጤና ግንዛቤ እና ቅድመ ጥንቃቄ

አዘውትሮ ምርመራ ማድረግ ጥያቄዎችን ለመጠየቅና መረጃ ለማግኘት ይረዳል። ዕጢ መኖሩ የእርስዎ ጥፋት ወይም የሰውነትዎ ድክመት አለመሆኑን ማስታወስ ይገባል። የሰውነት ለውጥ ተፈጥሯዊ ነው፤ ዕጢዎች እንዲሁም ሊከሰቱ ይችላሉ።

ግልጽና ትክክለኛ መረጃ ማግኘት በፍርሃት ከመውደቅ ይልቅ በእርጋታ ምላሽ ለመስጠት ያስችላል። ስለ ምልክቶችዎ ወይም ስለ ምርመራ ውጤትዎ እርግጠኛ ካልሆኑ ጥያቄዎችን መጠየቅ ኃላፊነት የተሞላበት እርምጃ ነው። ሁሉም መልሶች ወዲያውኑ ሊኖሩዎት አይገባም። በሰውነትዎ ውስጥ ምን እየተከናወነ እንዳለ ለመረዳት ጊዜ መውሰድ ለጤናዎ የሚበጀውን ውሳኔ ለማሳለፍ ይረዳዎታል።

የማህፀን ካንሰርን መለየት

አብዛኞቹ ዕጢዎች ካንሰር ባይሆኑም (benign)፣ አደገኛ የሆኑ ምልክቶችን መለየት ግን ወሳኝ ነው። የማህፀን ካንሰር በብዙ አካባቢዎች ከሚከሰቱ የካንሰር ዓይነቶች በ 4ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ከማህፀን በር እና ከጡት ካንሰር በመቀጠል ለሴቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት ካንሰሮች መካከል ደግሞ በ 3ኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል።

ሊጠፉ ከሚችሉት ተራ ዕጢዎች በተቃራኒ፣ የማህፀን ካንሰር ምልክቶች የማይለቁና እየባሱ የሚሄዱ ናቸው። ሊታወቁ የሚገባቸው የማስጠንቀቂያ ምልክቶች፦

● የማይለቅ የሆድ መንፋት።

● ምግብ እንደጀመሩ ወዲያውኑ የመጥገብ ስሜት።

● ያለ ምክንያት የሰውነት ክብደት መቀነስ።

● የሽንት ወይም የሰገራ አወጣጥ ለውጥ (ለምሳሌ ሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ወይም የሆድ ድርቀት)።

ለማህፀን ካንሰር ቀላል የሆነ መደበኛ የማጣሪያ ምርመራ (Screening test) ስለሌለ፣ የእርስዎ ንቁ መሆን ትልቁ መከላከያ መንገድ ነው። ከጥቂት ሳምንታት በላይ የሚቆይ አዲስ ወይም ያልተለመደ የዳሌ/ሆድ ሕመም ካለብዎት፣ የሕክምና ምርመራ ወይም አልትራሳውንድ ማድረግ ተገቢ ነው። ለጤናዎ ባለቤት መሆንዎ፣ የሚያጋጥመው ነገር ተራ ዕጢም ይሁን አስቸኳይ ሕክምና የሚያስፈልገው ጉዳይ፣ ለረጅም ጊዜ ጤናዎ ቅድሚያ እንዲሰጡ ይረዳዎታል።

 

You might have heard the term “ovarian cyst” and immediately thought something was seriously wrong. Or maybe it came up during a scan or conversation, leaving you unsure what it really means. This is a common reaction, today we explore what you need to know.

Ovarian cysts are fluid-filled sacs that develop on or inside the ovaries. In most cases, they are a normal part of how the body works. During each menstrual cycle, the ovaries prepare and release an egg. Sometimes, a small sac forms around the egg and does not disappear right away. These are called functional cysts, such as follicular or corpus luteum cysts. They usually go away on their own within one to three months without treatment. Most ovarian cysts are not dangerous and do not affect long-term health.

 Many ovarian cysts do not cause any symptoms at all. They are often discovered during routine checkups or ultrasounds done for other reasons. When symptoms do appear, they can include a feeling of heaviness in the lower abdomen, mild bloating, or a dull ache on one side. These signs can easily be confused with everyday menstrual discomfort. There are also less common types of cysts that are not related to the monthly cycle. For example, endometriomas are linked to a condition called endometriosis, where tissue similar to the lining of the uterus grows outside it. Dermoid cysts can contain different types of tissue such as skin or hair, and cystadenomas develop from the surface of the ovary. These types may need closer monitoring. Understanding that not all cysts are the same helps reduce confusion and prevents unnecessary fear.

Knowing when to seek medical care is important. Most cysts are harmless, but certain symptoms should not be ignored. Sudden and severe pelvic pain, especially if it comes quickly, needs urgent attention. Pain that is accompanied by fever or vomiting is another warning sign. In rare cases, a cyst can rupture or cause the ovary to twist, a condition known as torsion. Signs like rapid breathing, dizziness, or cold and clammy skin may indicate a more serious situation and require immediate care. If a cyst is found during an ultrasound, the usual approach is to monitor it over time. This is often called watchful waiting. Hormonal contraceptives may help prevent new cysts from forming, but they do not shrink existing ones. Surgery is only considered if a cyst is very large, persistent, or causing significant pain.

While most cysts are benign, it is vital to recognize when symptoms signal something more serious. Ovarian cancer is the 4th most common cancer in many regions and the 3rd leading cause of cancer-related deaths among women, following cervical and breast cancer. Unlike functional cysts that usually disappear, the signs of ovarian cancer are persistent and progressive. Warning signs to watch for include persistent abdominal bloating, feeling full quickly after eating (early satiety), unexplained weight loss, and changes in bowel or bladder habits, such as frequent urination or constipation.

 Because there is no simple routine screening test for ovarian cancer awareness is your most powerful tool. If you experience new or unusual pelvic discomfort that lasts for more than a few weeks, seeking a medical evaluation or an ultrasound is a responsible and necessary step. Taking ownership of these changes ensures that whether it is a harmless cyst or a condition requiring urgent intervention, you are making decisions that prioritize your long-term health and survival.

 

 

 

 

wpChatIcon