የጉርምስና ዕድሜ የመማሪያ፣ የማደጊያና ራስን የማወቂያ ጊዜ መሆን አለበት። በሚያሳዝን ሁኔታ ግን ብዙ ወጣት ሴቶች በአካላዊ ጤንነታቸው፣ በስነ-ልቦና ደህንነታቸው፣ በትምህርታቸውና በወደፊት ዕድላቸው ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድር ጥቃት ይደርስባቸዋል። የታዳጊዎች ጥቃት አካላዊ ጥቃትን፣ የስሜት በደልን፣ ጉልበተኝነትን፣ የወሲብ ጥቃትን፣ የኢንተርኔት ትንኮሳን፣ እንዲሁም በቤት ውስጥ፣ በትምህርት ቤት፣ በፍቅር ግንኙነትና በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጸሙ ጎጂ ልማዶችን ጨምሮ በብዙ መልኩ ሊገለጽ ይችላል።

በጉርምስና ዕድሜ ላይ የሚደርስ ጥቃት ዘላቂ የሆኑ መዘዞችን ሊያስከትል ይችላል። ጥቃት የደረሰባቸው ወጣቶች ለጭንቀት፣ ለድብርት፣ ለዝቅተኛ በራስ መተማመን እና ለሌሎች የስነ-አዕምሮ ጤና እክሎች የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። በትምህርታቸው ሊዳከሙ፣ ከማህበራዊ ህይወት ሊገለሉ፣ ለአደገኛ ባህሪያት ሊጋለጡ ወይም ለረጅም ጊዜ ለሚቆዩ የጤና እክሎች ሊዳረጉ ይችላሉ። በከፋ ሁኔታ ደግሞ ጥቃቱ ለአካል ጉዳት፣ ላልተፈለገ እርግዝና፣ ለአባላዘር በሽታዎች ወይም ለሞት ጭምር ሊዳርግ ይችላል።

ሴትና ወንድ ታዳጊዎች ጥቃትን የሚያስተናግዱበት መንገድ ብዙ ጊዜ ይለያያል። ሴት ታዳጊዎች የወሲብ ትንኮሳ፣ የፍቅር አጋር ጥቃት፣ የልጅነት ጋብቻና ጾታዊ ጥቃት ሊገጥማቸው የሚችል ሲሆን፤ ወንድ ታዳጊዎች ደግሞ ለአካላዊ ጥቃት፣ ከቡድን ጋር ለተያያዙ ጥቃቶችና ለጎጂ ማህበራዊ ጫናዎች የመጋለጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው። ሆኖም ግን ጥቃት እድሜ፣ ጾታ፣ አስተዳደግ ወይም ማህበራዊ ደረጃ ሳይለይ ማንኛውንም ወጣት ሊነካ ይችላል።

የዲጂታል ቴክኖሎጂ እድገት አዳዲስ የጥቃት ዓይነቶችንም ይዞ መጥቷል። የኢንተርኔት ጥቃት፣ እና የዲጂታል ትንኮሳ ታዳጊዎችን ከትምህርት ቤት አልፎ እስከ ቤታቸው ድረስ ሊከተላቸው ይችላል፤ ይህም አስተማማኝ ከለላ ለማግኘት አዳጋች ያደርገዋል። አብዛኛው የዚህ አይነት በደል በኢንተርኔት ላይ ስለሚፈጸም፣ ብዙ ጊዜ በወላጆች፣ በአስተማሪዎችና በሌሎች ሰዎች ሳይስተዋል ይቀራል።

የታዳጊዎችን ጥቃት መከላከል ከቤተሰብ፣ ከትምህርት ቤቶች፣ ከማህበረሰቡና ከመንግስት የተቀናጀ እርምጃን ይጠይቃል። ደህንነቱ የተጠበቀ አካባቢ መፍጠር፣ እርስ በርስ መከባበር ያለበትን ግንኙነት ማሳደግ፣ የጥቆማ ሥርዓቶችን ማጠናከር እና ለወጣቶች ምቹ የሆኑ የድጋፍ አገልግሎቶችን መስጠት ወጣቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ ይረዳል። ስለ ስምምነት፣ ጤናማ ግንኙነትና ስለ ግል ደህንነት ግልጽ የውይይትና የትምህርት መድረኮችን ማዘጋጀትም ጥቃትን ለመቀነስና ወጣቶች በሚፈልጉበት ጊዜ እርዳታ እንዲጠይቁ ለማስቻል ወሳኝ እርምጃዎች ናቸው።

እያንዳንዱ ታዳጊ ከፍርሃት፣ ከበደልና ከጥቃት ነፃ በሆነ አካባቢ የማደግ መብት አለው። የወጣቶችን ድምጽ በመስማት፣ የተጎዱትን በመደገፍና የጥቃቱን መንስኤዎች በመቅረፍ ታዳጊዎች ሊያድጉና ሊበለጽጉ የሚችሉባቸውን ጤናማና ደህንነታቸው የተጠበቀ ማህበረሰቦችን መፍጠር እንችላለን።

Adolescence should be a time of learning, growth, and self-discovery. Unfortunately, many young people experience violence that affects their physical health, mental well-being, education, and future opportunities. Adolescent violence can take many forms, including physical violence, emotional abuse, bullying, sexual violence, online harassment, and harmful practices within homes, schools, relationships, and communities.

Violence during adolescence can have lasting consequences. Young people who experience violence are more likely to develop anxiety, depression, low self-esteem, and other mental health challenges. They may struggle academically, withdraw from social activities, engage in risky behaviors, or face long-term health problems. In severe cases, violence can result in injury, unwanted pregnancy, sexually transmitted infections, or even death.

Girls and boys often experience violence differently. Adolescent girls may face sexual harassment, intimate partner violence, child marriage, and gender-based violence, while boys are more likely to experience physical violence, gang-related violence, and harmful social pressures. However, violence can affect any young person regardless of age, gender, background, or social status.

The rise of digital technology has also introduced new forms of violence. Cyberbullying, online exploitation, and digital harassment can follow adolescents beyond school and into their homes, making it difficult to find safe spaces. Because much of this abuse happens online, it often goes unnoticed by parents, teachers, and caregivers.

Preventing adolescent violence requires action from families, schools, communities, and governments. Creating safe environments, promoting respectful relationships, strengthening reporting systems, and providing youth-friendly support services can help protect adolescents from harm. Open communication and education about consent, healthy relationships, and personal safety are also essential in reducing violence and empowering young people to seek help when needed.

Every adolescent deserves to grow up in an environment free from fear, abuse, and violence. By listening to young people, supporting survivors, and addressing the root causes of violence, we can help create healthier, safer communities where adolescents can thrive.

 

wpChatIcon