እርግዝና አስደሳች ጉዞ ነው፤ ነገር ግን እንደ አጋጣሚ ሆኖ እያንዳንዱ እርግዝና መጨረሻው እንደተጠበቀው ላይሆን ይችላል። ውርጃ ወይም በራሱ የሚከሰት የፅንስ መቋረጥ የሚባለው፣ እርግዝናው 20 ሳምንት ሳይሞላው ሲቋረጥ ነው። ምንም እንኳን የፅንስ መቋረጥ በስነልቦና ጫና ረገድ በጣም አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም፣ ብዙ ሰዎች ከሚያስቡት በላይ በተደጋጋሚ የሚያጋጥም እና ብዙውን ጊዜ በማንም ሰው ቁጥጥር ስር ባልሆኑ ምክንያቶች የሚከሰት ነው።
ለፅንስ መቋረጥ የተለመደው ምክንያት ከፅንሱ ክሮሞዞም ጋር የተያያዘ ችግር ነው። ክሮሞዞሞች የዘረመል (ጄኔቲክ) መረጃዎችን የሚሸከሙ ሲሆን፣ በፅንስ መፈጠር ወይም በቅድመ-ሕዋስ ክፍፍል ወቅት የአካል ጉድለቶች ሲከሰቱ እርግዝናው በተገቢው ሁኔታ ላይቀጥል ይችላል። አብዛኛውን ጊዜ፣ እነዚህ የዘረመል ለውጦች በአጋጣሚ የሚከሰቱ እንጂ በወላጆች ምክንያት የመጡ አይደሉም።
አንዳንድ የጤና እክሎችም የፅንስ መቋረጥ አደጋን ሊጨምሩ ይችላሉ። በአግባቡ ያልተቆጣጠሩት የስኳር በሽታ፣ የታይሮይድ እጢ ችግሮች፣ የሆርሞን መዛባት፣ አንዳንድ ኢንፌክሽኖች፣ የሰውነት ራሱን የመከላከል አቅም እክሎች ፣ እና የማህፀን ወይም የማህፀን በር ችግሮች ለፅንስ መቋረጥ አስተዋፅዖ ሊያደርጉ ይችላሉ። በአንዳንድ ሁኔታዎች ደግሞ እንደ ሲጋራ ማጨስ፣ ከልክ ያለፈ የአልኮል መጠጥ መጠጣት፣ ሱሰኛ የሚያደርጉ ዕጾችን መጠቀም፣ ወይም ለጎጂ ኬሚካሎች በከፍተኛ ሁኔታ መጋለጥ ያሉ የኑሮ ዘይቤዎች አደጋውን ሊጨም ይችላሉ።
ዕድሜ ሌላው ከግምት ውስጥ ሊገባ የሚገባ ጉዳይ ነው። ሴቶች ዕድሜያቸው እየገፋ ሲሄድ፣ በተለይም ከ35 ዓመት በኋላ፣ የክሮሞሶም እክሎች የመከሰት ዕድላቸው ስለሚጨምር የፅንስ መቋረጥ ይበልጥ የተለመደ ይሆናል። ሆኖም ግን የፅንስ መቋረጥ በማንኛውም የመውለጃ ዕድሜ ክልል ውስጥ ሊከሰት እንደሚቻል ማወቅ ተገቢ ነው።
እንደ መራመድ፣ መስራት፣ ተስማሚ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ በጤናማ እርግዝና ወቅት የግብረ-ሥጋ ግንኙነት መፈጸም፣ ወይም የተለመደ የስሜት ውጥረትን ማስተናገድ ያሉ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎች አብዛኛውን ጊዜ ለፅንስ መቋረጥ መንስኤ እንደማይሆኑ መረዳት በጣም አስፈላጊ ነው። ብዙ ሰዎች ፅንስ ከተቋረጠ በኋላ ራሳቸውን ይወቅሳሉ፤ ነገር ግን በአብዛኛዎቹ ሁኔታዎች ይህንን ለመከላከል ሊያደርጉት የሚችሉት ምንም ነገር እንዳልነበረ ማወቅ አስፈላጊ ነው።
የፅንስ መቋረጥ ምልክቶች፦ ከማህፀን ደም መፍሰስ፣ ቁርጠት ወይም የሆድ ህመም፣ የሕብረ ህዋስ (tissue) ወይም የደም መርጋት መውጣት፣ እና የእርግዝና ምልክቶች በድንገት መጥፋት ናቸው። ይሁን እንጂ ቀላል ደም መፍሰስ ማየት ሁልጊዜ የፅንስ መቋረጥ እየተከሰተ ነው ማለት አይደለም። በእርግዝና ወቅት ደም መፍሰስ ወይም ከፍተኛ ሕመም ካጋጠመ ማንኛውም ሰው በአስቸኳይ የሕክምና ምርመራ ማግኘት አለበት።
ምንም እንኳን ሁሉንም የፅንስ መቋረጦች መከላከል ባይቻልም፣ ከእርግዝና በፊት እና በእርግዝና ወቅት ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን መከተል የተወሰኑ አደጋዎችን ለመቀነስ ይረዳል። መደበኛ የቅድመ-ወሊድ ክትትል ማድረግ፣ የፎሊክ አሲድ ንጥረነገርን መውሰድ፣ ሥር የሰደዱ የጤና እክሎችን መቆጣጠር፣ ከማጨስና ከአልኮል መራቅ፣ እና የጤና ባለሙያዎ የሚሰጡትን ምክሮች መከተል ሁሉም ለበለጠ ጤናማ እርግዝና አስተዋፅዖ ያደርጋሉ።
አንድ ጊዜ የፅንስ መቋረጥ ማጋጠሙ የግድ የወደፊት እርግዝናዎች ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል ማለት አይደለም። ፅንስ የመቋረጥ ችግር አጋጥሟቸው የነበሩ አብዛኞቹ ሴቶች በቀጣይ ጤናማ እርግዝና ይኖራቸዋል። አንድ ሰው በተከታታይ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የፅንስ መቋረጥ ካጋጠመው፣ ተጨማሪ ምርመራ ወይም ሕክምና የሚያስፈልግ መሆኑን ለመወሰን ከጤና ባለሙያ ጋር መማከር አለበት።
የፅንስ መቋረጥ ምልክቶች ካጋጠሙዎት ወይም በእርግዝና ወቅት ስጋቶች ካሉዎት፣ በተቻለ ፍጥነት የሕክምና ክትትል ማግኘት ተገቢውን ምርመራ፣ ሕክምና እና የስሜት ድጋፍ ለማረጋገጥ ይረዳል። የፅንስ መቋረጥ በተደጋጋሚ የሚያጋጥም መሆኑን እና በዚህ አስቸጋሪ ተሞክሮ ውስጥ ለሚያልፉ ሰዎች ድጋፍ መኖሩን ያስታውሱ።
Pregnancy is an exciting journey, but unfortunately, not every pregnancy continues as expected. A miscarriage, also known as a spontaneous pregnancy loss, is the loss of a pregnancy before 20 weeks of gestation. While miscarriages can be emotionally difficult, they are more common than many people realize and are often caused by factors beyond anyone’s control.
The most common cause of miscarriage is a problem with the baby’s chromosomes. Chromosomes carry genetic information, and when there are abnormalities during fertilization or early cell division, the pregnancy may not develop normally. In most cases, these genetic changes happen by chance and are not caused by anything the parents did.
Certain maternal health conditions can also increase the risk of miscarriage. Poorly controlled diabetes, thyroid disorders, hormonal imbalances, some infections, autoimmune conditions, and abnormalities of the uterus or cervix may contribute to pregnancy loss. In some cases, lifestyle factors such as smoking, excessive alcohol consumption, recreational drug use, or significant exposure to harmful chemicals may also increase the risk.
Age is another important factor. As women get older, particularly after the age of 35, the likelihood of chromosomal abnormalities increases, making miscarriage more common. However, miscarriage can occur at any reproductive age.
It is important to understand that everyday activities such as walking, working, exercising appropriately, having sexual intercourse during a healthy pregnancy, or experiencing normal emotional stress do not usually cause miscarriage. Many people blame themselves after a pregnancy loss, but in most cases, there was nothing they could have done to prevent it.
Common symptoms of a miscarriage include vaginal bleeding, cramping or abdominal pain, passing tissue or blood clots, and the sudden disappearance of pregnancy symptoms. However, light bleeding or spotting does not always mean a miscarriage is occurring. Anyone experiencing bleeding or severe pain during pregnancy should seek medical evaluation promptly.
Although not all miscarriages can be prevented, maintaining a healthy lifestyle before and during pregnancy may help reduce certain risks. Regular prenatal care, taking folic acid, managing chronic medical conditions, avoiding smoking and alcohol, and following your healthcare provider’s recommendations all contribute to a healthier pregnancy.
Experiencing one miscarriage does not necessarily mean future pregnancies will be affected. Most women who have had a miscarriage go on to have healthy pregnancies. If someone experiences two or more consecutive miscarriages, they should speak with a healthcare provider to determine whether additional evaluation or treatment is needed.
If you experience symptoms of a miscarriage or have concerns during pregnancy, seeking medical care as soon as possible can help ensure appropriate evaluation, treatment, and emotional support. Remember that pregnancy loss is common, and support is available for those going through this difficult experience.